የአረንጓዴ አሻራ ብሔራዊ መርሃ ግብር ግድቦቻችን በደለል እንዳይሞሉ ለማድረግና የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ውኃ ግኝታችን እንዲጎለብት አዎንታዊ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለፀ፡

ሀምሌ 15/2018 ዓ.ም
ለገዳዲ
*******************®****************
የኢትዮጵያ ደን ልማት አመራሮችና ሠራተኞች በኦሮሚያ ክልል በሸገር ሲቲ ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ በኩራ ጂዳ ወረዳ በለጋዳዲ የውኃ ግድብ ተፋሰስ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አከናወኑ።
ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ከሚገኙ ታላላቅ የልማት ፕሮግራሞች መካካል አንዱ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ሲሆን በመርሃ ግብሩም እስከዚህ አመት ክረምት መግቢያ ድረስ ከ48 ቢሊዮን በላይ የተለያየ ፋይዳ ያላቸው ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋናችንን ማሳደግ ተችሏል፡፡ በያዝነው የክረምት ወራትም 8 .5 ቢሊዮን ያህል ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸው ታቅዶ ለተግባራዊነቱ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በርካታ ሀገራዊ ፋይዳዎችን እያስገኘ ሲሆን የተራቆቱ መሬቶች መልሰው እንዲያገግሙ፤ የአፈር መሸርሽርን መከላከል፤ በዘርፉ በርካታ የስራ እድል በመፍጠር የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፤ የከርሰ እና የገፀ ምድር ውሀ ግኝታችን እንዲያድግ ማድረግ፣ የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን መቀነስ፣ የስርዐተ ምዳርና የብዝሀ ህይወት ሀብቶቻችን እንዲጠበቁ ማድረግ እና ሌሎች በርካታ ቀጥተኛ ያልሆኑ ፋይዳዎችን እያስገኘ ነው።
የኢትዮጵያ ደን ልማት ተቋም የአረንጓዴ አሻራን መርሀ ግብር በሀገር ደረጃ በቴክኒክ ከመምራት በተጨማሪ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ከመምራት፣ ከማስተባባርና የተለያዩ የሎጅስቲክስና የሀብት ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ እንደ ተቋም በዋናው መስሪያ ቤትና በክልሎች በሚገኙ ማዕከላት ደረጃ በየአመቱ ቀርካታ ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ ላይ ይገኛል።
በዚሁ መሠረት በዛሬው ዕለት በተቋሙ ዋና መ/ቤትና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ማዕከል የሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞች በሸገር ሲቲ ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ በኩራ ጂዳ ወረዳ ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት የለገዳዲ የውኃ ግድብ በደለል እንዳይሞላ እና በዙሪያው እየተሰሩ ያሉ የአፈርና ውኃ እቀባ ስራዎችን በችግኝ ለማጠናከር የሚያስችል ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ 15 ሺህ 600 የሀገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል፡፡
በችግኝ ተከላው ማስጀመሪያ ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ከበደ ይማም ለሠራተኞች ባስተላለፉት መልእክት እንዳሉት “የአረንጓዴ አሻራ ብሔራዊ መርሃ ግብር ግድቦቻችን በደለል እንዳይሞሉ ለማድረግና የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ውኃ ግኝታችን እንዲጎለብት አዎንታዊ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው” ብለዋል፡፡
ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ አክለው እንዳሉት “በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንከብካቤ ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ ረገድ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ገልፀው ይህ ሀገራዊ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የታለመለትን ውጤት እንዲያሳካ የዘርፉ ባለሞያዎች ድርብ ሀላፊነት እንዳለባቸው በማሰብ በትጋት የተጀመረውን ጥረት እንዲደግፉ አደራ ብለዋል።
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የተፋሰስ አስተዳደር ጥበቃና ማኔጅመንት ዲቪዥን ኃላፊ አቶ ሙልጌታ ታዬ በተከላው ወቅት እንዳሉት “የለጋዳዲ የውኃ ግድብ በደለል እንዳይሞላ እየተሰሩ ያሉ የተፋሰስና የልማት ስራዎችን በአትክልትና ፍራፍሬ እየለሙ እና ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን ገልፀው ቀጣይ ከባለድርሻዎች ጋር በመተባባር ግድቡን ለመጠበቅ ተከታታይነት ያለው ስራ እንደሚሰራ ተናግረው ከዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ደን ልማት እንደ መሪ ተቋም በቅንጅት አብሯቸው እንዲሰራ ጥሪ አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም ባለስልጣን መ/ቤቱ በመጠጥ ወሀ ማቆሪያው ዙሪያ የሠራቸው የአፈርና ውሀ ጥበቃና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተጎብኝቷል
May be an image of one or more people and treeMay be an image of one or more people and grass

Related posts