“ጊዜዬን፣ ጉልበቴንና ሀብቴን አፍስሼ በሰራሁት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የደን ልማት ስራ እንደ ግለሰብ ምድርን ለመታደግ በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የራሴን አዎንታዊ አስተዋፅኦ በማበረከቴ ደስተኛ ነኝ” ። “አርሶ አደር ክፍሌ ሌማን

ጳጉሜ 2026፤ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ
ደቡብ ሶዶ ወረዳ ጉልቤ ቀበሌ(ኢ.ደ.ል)
********************®******************
ከአዲስ አባባ 120 ኪ.ሜ ተጉዘን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፤ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ ጉልቤ ቀበሌ ተገኝተናል፡፡ የጉዟችን ዓላማ በደንና ተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ስራ ለበርከታ ዓመታት የተጎዳና የተጎሳቆለ መሬት መልሶ እንዲያገግምና ጥቅም ላይ እንዲውል ያለመታከት እየሰሩ የሚገኙትን የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ ደን አደርና አርሶ አደር የሆኑትን አቶ “ጊዜዬን፣ ጉልበቴንና ሀብቴን አፍስሼ በሰራሁት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የደን ልማት ስራ እንደ ግለሰብ ምድርን ለመታደግ በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የራሴን አዎንታዊ አስተዋፅኦ በማበረከቴ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል፡፡ን መልካም ስራና ውጤት (ተሞክሮ) አይተን በማሳየት ለተደራሾቻችን ልምድ ለማጋራት ነው፡፡
የደን ልማትና የተፈጥሮ ሀብት እንዲሁም የሰብል ምርቶች አርሶ አደር የሆኑት አቶ ክፍሌ ሌማን በቀለም ትምህርት 12ኛ ክፍልን አጠናቀዋል። ይሁንና እ.ኢ.አ. ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ለደን ልማትና ጥበቃ ስራ ሙሉ ጊዜያቸውን በመስጠት ለበርካታ ዘመናት ተደጋግሞ በመታረሱ ምከንያት ለምነቱን አጥቶ የተጎሳቆለውን የእርሻ ማሳቸውን መልሶ በመንከባከብና በማልማት አካባቢያቸውን ለመቀየር ቆርጠው እንዲነሱ ምክንያት እንደሆናቸው ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል።
አቶ ክፍሌ ያለፈ ጊዜ የደን ጭፍጨፋና ምንጣሮ ትዝታቸውን በቁጭት ሲነግሩን እንዳሉት “ቀደም ሲል ደኖችን ከማልማት ይልቅ ባልተገባ መንገድ እንዲጨፈጨፉና እንዲመነጠሩ በማድረጋችን የራሳችንን፣ የአካባቢያችንን እና የሀገራችንን የአካባቢ መራቆትና የኑሮ ሁኔታ መጎሳቆልን ነው ያተረፍነው!” ሲሉ በፀፀት ነግረውናል።
እንደ አቶ ክፍሌ ገለፃ የአካባቢያቸውን ደን በመጨፍጨፋቸውና ወደ ምድረ በዳነት በመቀየራቸው ምክንያት “ለከፋ ያልተለመደ የአየር ጠባይ መለዋወጥ፤ ለተደጋጋሚ ድርቅ፤ ወቅቱን ላልጠበቀ አደገኛ ዝናብና ጎረፍ፣ እንዲሁም ለመሬት መራቆትና በጎርፍ የለም አፈር መከላት ችግር እንድንጋለጥ አድርጎናል” ብለዋል፡፡
የችግሩን መፍትሄ አስመልክቶ ለጠየቅናቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡን አቶ ክፍሌ እንዳሉት “የዚህን መሠል ችግር ተጋለጭነት ለመቀነስ የእያንደንዱ ዜጋ ቁርጠኝነትና በተግባር የተደገፈ ምላሽ ያስፈልጋል፣ ለዚህ ደግሞ እኔ ህያው ምስክር ነኝ” ብለዋል።
በማሳቸው ላይ ተገኝተን እንደተመለከትነው አቶ ከፍሌ ከአራት ሄክታር በላይ የሆነ፣ የተጎዳና የተጎሳቆለ የእርሻ መሬታቸውን መልሶ ለማልማትና ወደ ነበረበት ለመመለስ ከሃያ ዓመታት በላይ እንደፈጀባቸውና አሁን ላይ የአከባቢውን ስርዓተ ምዳር በመለወጥ የተሞክሮ ማዕከልን ለመሆን የበቁ ታታሪ አርሶና ደን አደር ናቸው።
አርሶ አደሩ ባከናወኑት የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራቸው ከ97 በመቶ በላይ የተጎዳና የተጎሳቆለ መሬት መልሶ እንዲያገግም በማድረጋቸው ከ60 በላይ የእፅዋት ዓይነቶች፣ ከ18 በላይ ለመድኃኒትነት የሚያገለግሉ እፅዋቶች፣ በርካታ የብዝሀ ህይወታት እንዲሁም ከአካባቢው ጠፍቶ የነበረውን የሬዛ እንስሳ ዝርያ በዚሁ በተፈጥሮ ደን ውስጥ ተመልሰው እንዲገቡ ሆኗል።
አልሚው ለስራ ክፍላችን በሰጡት መጠይቅ እንዳሉት “ጊዜዬን፣ ጉልበቴንና ሀብቴን አፍስሼ በሰራሁት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የደን ልማት ስራ እንደ ግለሰብ ምድርን ለመታደግ በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የራሴን አዎንታዊ አስተዋፅኦ በማበረከቴ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል፡፡
የደን መኖር ለኢትዮጵያ ዋስትና መሆኑን የገለፁት አርሶ አደር ክፍሌ እንዳሉት “አባቶቻችን ‘በጠላት’ ወረራ ጊዜ ትልልቅ ዛፎችን እንደ ከለላ ተጠቅመው ራሳቸውን ከጠላት ጥይትና ጥቃት እንዳዳኑ ሁሉ በአሁኑ ጊዜ የደን መጠበቅ የታዳሽ ኃይል ለሆነው ከውሀ የመብራት ሀይል ለማመንጨት በማገልገል በጎረቤት ሀገራት ተሰሚነትና የኃይል ሚዛንን ለማስጠበቅ የሚያገለግል ዘርፍ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
የተጎሳቆሉና የተጎዱ መሬቶች እንዲያገግሙ በማድረግ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በንብ ማነብ፣ ለእሰሳት መኖነት የሚውሉ እፅዋቶችን በመትከል የአካባቢውን ስርዓተ ምህዳር ከመጠበቅ ባለፈ አርሶ አደሩ ከደንና ደን ውጤቶች ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱ የሀገራችን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተምሳሌታዊነቷን ለማረጋገጥ የተጀመረው አካባቢን የመጠበቅና የማልማት ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
May be an image of grass and tree

Related posts