ጳጉሜ / 2018 ዓ.ም
ሲዳማ ክልል፤ ይርጋለም ወረዳ
******************®****************
በሲዳማ ክልል ይርጋለም ወረዳ “የቻንኪ” የደን ምርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የሚሰሩ የአካባቢው ወጣቶች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ገለፁ፡፡
የማህበረሰቡ የአኗኗር ዘይቤ መቀየርና የህዝብ ቁጥር በመጨመሩ እንደ የቢሮ እና የቤት ቁሳቁስ ያሉ እንጨት ውጤቶች ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ የፋብሪካዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
በኢትዮጵያ ያለውን የደን ጥሬ እቃ አቅርቦት ምቹ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የተለያዩ የእንጨት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በሃገር ውስጥ ባለሃብቶች እና በውጭ ኢንቨስተሮች ተከፍተዋል፡፡
የሀገር ውስጥ የደን ውጤቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ መምጣታቸው ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ያላቸው ፋይዳ እጅግ የላቀ ነው። እነዚህ ተቋማት የእንጨትን ምርቶች በማቀነባበር ጥሬ እቃውን ወደ ምርትነት በመለወጥ የውጭ ምንዛሬን ለማዳን እና በውጭ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት በእጅጉ ለመቀነስ ያስችላሉ።
በተጨማሪም በገጠር እና በከተማ አካባቢዎች ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ወጣቶች ሰፊ ቋሚና ጊዜያው የስራ እድሎችን በመፍጠር የድህነት ቅነሳ ጥረቶችን በቀጥታ ይደግፋሉ፡፡ የሀገር ውስጥ ገበያን በታቀደና በተደራጀ መንገድ ለማስተሳሰር ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
በሲዳማ ክልል ይርጋለም ወረዳ የቻንኪ የደን ምርት ከሚያቀነባበሩ ፋብሪካዎች አንዱ ነው፡፡ ይህ ፋብሪካ በክልሉና ከአጎራባች ክልሎች የባህር ዛፍ እንጨትን በመግዛት ፕለይ ውድ በማምረት ላይ ይገኛል፡፡
ወጣት አማኑኤል ደምሴ በፋብሪካው በአስተባባሪነት እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን ፋብሪካው ለአካባቢው 116 ( ወ 80 ሴ 36 ) ለሚሆኑ ስራ አጥ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በሌላ በኩል ግንድ ለሚቆርጡ፣ ለሚያጓጉዙ እና ለጫኝ አውራጆችም የስራ እድል መፈጠሩን ጠቅሰው ደን ባይኖር እነዚህን የመሳሰሉ የስራ እድሎች ማግኝት አይችልም ነበር ብለዋል፡፡
የፋብሪካው ዋና አስተዳዳሪ ዥዋን ጁንግ በኢትዮጵያ የጥሬ እቃ አቅራቦትና ሰፊ የገበያ ፍላጎት በመኖሩ ወደ ስራው እንዲሰማሩ እንዳደጋቸው ጠቅሰው ያለውን የእንጨት ውጤቶች ፍላጎት ለመሸፈንና ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በማደን በኩል የበኩላቸውን ማበርከት እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡
ይህ ፋብሪካ ከተቋቋበት ዋንኛ አለማ በተጨማሪ ለአካባቢው ማህበረሰብ የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ነግረውናል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ ለሃያ የአካባው ነዋሪች አመታዊ የጤና መድን ዋስተና በድርጅቱ በኩል የተገዛላቸው መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡

