በዘንደሮው የክረምት ወራት በአረንጓዴ አሻራ ብሔራዊ መርሃ ግብር ለመትከል ከታቀደው ችግኞች 4.7 ቢሊዮን ያህል መተከሉ ተገለፀ፡

ሀምሌ 17/2018 ዓ.ም
*************®**************
የኢትዮጵያ ደን ልማት አመራሮችና ሠራተኞች የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፀፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ አካሄዱ፡፡
በእቅድ አፈፃፀምና ትውውቅ መድረኩ ተቋሙ በበጀት አመቱ ለማሳካት ያቀደውን እቅድ የፊዚካል ስራዎች 98.6% እንዲሁም በካፒታል በጀት አፈፃፀም 99.4% በአማካይ ደግሞ የዕቅዱን 94.4% በማከናወን ከፍተኛ አፈፃፀም አስመዝግቧል።
በበጀት አመቱ ለማከናወን የተያዙት ግቦች በሙሉ ከዘጠና ፐርሰንት በላይ አፈፃፀም የተመዘገበባቸው ሲሆን በተለይም ለልማት የሚውል ሀብት ከተለያዩ አካላት ከማፈላለግ አኳያ፣ የደን ሽፋንን ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶችን ከማሳካት ረገድ፣ ከደን ዘርፍ ህግ ተከባሪነት ረገድ፣ የደን ሀብት ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠርና ለዜጎች ገቢ ከማስገኘት ብሎም ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት አዎንታዊ አበርክቶ ከማድረግ አኳያና በተቋማዊ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ረገድ እና በሌሎችም ስራዎች ጥሩ አፈፃፀም ስለመመዝገቡ በግምገማው ተነስቷል።
በሀገራችን ላለፉት 7 አመታት ሲከናወን የቆየው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እስከዚህ ክረምት ደረስ ከ48ቢሊዮን የተለያየ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች የተተከሉ ሲሆነ በዘንድሮው የክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ ብሔራዊ መርሃ ግብር ከ 8.5 ቢሊዮን ያህል ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እስከዛሬ ቀን ድረስ 4.7ቢሊዮነ ችግኞች ስለመተከላቸው ከክልሎች የተጠናቀረው መረጃ አመላክቷል።
የውይይት መድረኩን ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ከበደ ይማም እንዳሉት “የኢትዮጵያ ደን ልማት በዕቅድ አፈፃፀሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እምርታዊ ለውጦችን እያስመዘገበ መምጣቱን ገልፀው በተለይም የአረንጓዴ አሻራ ብሔራዊ መርሃ ግብር እንደ ሀገር የተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገ በመምጣቱ በያዝነው በዚህ የክረምት ወራት የተቀናጀ የህዝብ ተሳትፎና ንቅናቄ በማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ርብርብ እየተደረገ ነው” ብለዋል።
የተቋሙ ሠራተኞች በቀረበው እቅድ አፈፃፀም ረፖርት እና እቅድ ላይ ጥያቄና አስተያየት አቅረበው በሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች ተጨማሪ ገለፃና ማብራሪያ የተሠጠ ሲሆን መድረኩን መርተው ያጠቃለሉት ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ በቀጣይ የትኩረት ጉዳዮች ላይም አመራርና አቅጣጫ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል።

May be an image of one or more people and people studying

Related posts