1. በኢትዮጵያ ደን ልማት የጽ/ቤት ኃላፊ ዓላማ፡–
በኢትዮጵያ ደን ልማት ለጽ/ቤቱ የተሰጡ ሥራዎችን በመምራት፣ ውሳኔ የተሰጣቸውን ጉዳዮች አፈጻጸም በመከታተል፣ የተጠሪ ተቋማት አደረጃጀቶች እንዲጠናከሩ ድጋፍ በማድረግ፣ የአሠራር ሥርዓት በመቀየስና አፈፃፀማቸውን በመገምገም የተቋሙን ግቦች እንዲሳኩ ማድረግ ነው ።
2. የጽ/ቤቱን ሥራዎች ማቀድ፣ማስተባበር፣መምራት፣
የጽ/ቤቱን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፣ የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል። በተቋሙ ስትራቴጂክ የዕቅድ ዝግጅት ሂደት ከማኔጅመንት አካላት ጋር በመቀናጀት የዋና ዋና ተግባራት የአፈጻጸም አቅጣጫዎች ተካተው እንዲዘጋጁ ያደርጋል። የተቋሙን ተልዕኮ ከማሳካት አንጻር ችግሮችን ይለያል፣መፍትሔ እንዲያገኙ ተገቢውን ክትትል ያደርጋል ።
ጽ/ቤቱን አስመልክቶ በየጊዜው ለበላይ አካላትና ለተለያዩ መ/ቤቶች የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን ይከታተላል፣ ለጽ/ቤቱ ዓመታዊ ዕቅድ የሚያስፈልግ በጀትና ግብዓቶች በዕቅድ መዘርዘራቸውን ይከታተላል፣ የፕሮግራም ክንውንና አጠቃላይ የበጀት አጠቃቀምን አስመልክቶ አፈጻጸሙን በጋራ ይገመግማል።
ለጽ/ቤት የሚያስፈልግ የሰው ኃይልና የሰው ሀብት ልማት ዕቅድ በማዘጋጀት የፈጻሚ አካላትን አቅም ለማሳደግ የበጀትና የስራ ግብዓቶች ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ ያደርጋል። በሥራ ክፍሎች መካከል የተቀናጀ የሃብት አጠቃቀምና የሥራ ሥምሪት አሠራር እንዲኖር በማድረግ ተቋማዊ ውጤታማነትን በመከታተልና በመደገፍ ያረጋግጣል።
በስሩ የሚገኙ ኃላፊችና ሰራተኞች የሥራ አፈፃፀም በየምዕራፉ ይገመግማል፣ የተጠቃለለ የምዘና ሪፖርቶችን ያቀርባል። በሥራ ክፍሉ ውስጥ የቡድን ስሜትና ተነሳሽነት እንዲፈጠርና በዘላቂነት እንዲቀጥል ተገቢውን አመራር ይሰጣል። በሥራ ክፍሉ የሚገኙ ልዩ ልዩ ሰነዶችን በአግባቡ ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ሆነው እንዲደራጁ ያደርጋል።
3. ውሳኔ የተሰጣቸውን ጉዳዮች አፈጻጸም መከታተል፣
በበላይ አመራሩ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን ከህግና መ/ቤቱ ከተሰጠው ተግባርና ሀላፊነት አንፃር በመለየት በማስረጃ ተደግፈው እንዲቀርቡ ያደርጋል፣ ተፈጻሚነታቸውም ክትትል ያደርጋል፣ ውጤቱንም ለአመራሩ ያቀርባል።ከተጠሪ ተቋማት እንዲሁም ከውጪ ለመ/ቤቱ የሚላኩ ጉዳዮችን በማየት በራሱ ለሚፈጸሙት ምላሸ ይሰጣል፤
ከበላይ አመራሩ ወደ ተለያዩ የሥራ ክፍሎች የሚመሩ ደብዳቤዎችንና ልዩ ልዩ ጉዳዮችን በተሰጠው ውክልና መሠረት መፈጸሙን ይከታተላል፡፡ለተለያዩ አካላት የሚጻፉ መልዕክቶችንና ደብዳቤዎችን አዘጋጅቶ ለሃላፊው ያቀርባል። ከጽ/ቤቱ ወጪ የሚሆኑ ደብዳቤዎችን፣ ሰርኩላሮችንና መመሪያዎችን ለሚመለከታቸው አካላት መሰራጨታቸውን ያረጋግጣል፡፡
በመ/ቤቱና በሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚደረጉ የፕሮቶኮል ስምምነት ሰነዶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንዲዘጋጅና እንዲፈጸም ይከታተላል ።
በበላይ አመራሩ ሰብሳቢነት ለሚካሄዱ ስብሰባዎች አጀንዳዎችን በመለየት አዘጋጅቶ ለተሰብሳቢዎች እንዲበተን ያደርጋል፤ የስብሰባ ቃለ ጉባኤዎችን ይይዛል ወይም እንዲያዝ ያደርጋል፣ ቃለጉባኤውን ለሥራ ክፍሎችና ለሚመለከታቸው አካላት ይልካል፣ የተሰጡ ውሳኔዎችን እና አቅጣጫዎችን ተፈጻሚነት ይከታተላል።
4. ተጠሪ ተቋማት አደረጃጀቶች እንዲጠናከሩ ድጋፍ ማድረግ፣
የተጠሪ ስራ አስፈጻሚ የክፍላቸውን እቅድ ተጣጣሚነት ያለው ሆኖ እንዲዘጋጅ፣ እንዲተገበርና የአፈጻጸም ውጤታማነቱም ወጥነት እንዲኖረው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ይሰራል፣ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል ።የተቋሙ ተልዕኮ ውጤታማ እንዲሆን ከሚመለከታቸው የውስጥና የውጭ አካላት ጋር ግንኙነት ያደርጋል፣ ይደግፋል፣ በመመካከር አዳዲስ የአሰራር ዘዴዎችን ይቀርጸል ።
5. በጽ/ቤት ስር የሚከናወኑ ተግባራትን ማስተባበርና መምራት መገምገም፣ መቆጣጠር፣ ማረጋገጥ፤
በተቋሙ የፋይናንሻል፣ የክዋኔ እና ፐርፎርማንስ ኦዲት እንዲከናወኑ ያደርጋል፣ የኦዲት ግኝቶች መሰረት በማድረግ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡የተቋሙ ሂሳብ በውጭ/በዋና ኦዲት እንዲመረመር ያደርጋል፣ በተሰጡ ግኝቶች ላይ የማስተካከያ እርምት እርምጃዎች እንዲወሰድ በማድረግ ያረጋግጣል፡፡የኦዲት ሥራዎች የኦዲት ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ይከታተላል፣ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ እንቅስቃሴዎችን በመከታተል በመስሪያ ቤቱ ተግባራት ላይ የሚኖራቸውን እንደምታ ለሥራ አመራሩ ያሳውቃል፡፡
የተቋሙን ገጽታ ለመገንባት የሚረዱ ሁነቶችን እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ በሁነቱ ላይ ትክክለኛ መልዕክት እንዲተላለፉ መደረጉን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል ተቋሙን ገጽታ ለመገንባት የሚረዱ ዶክመንተሪ ፊልሞች እንዲዘጋጁና እንዲሰራጩ መደረጉን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል
የመንግስት ሃብትና ንብረት አቅርቦት፣ አደረጃጀት፣ ስርጭትና አጠቃቀም አግባብነት ባላቸው ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት እየተከናወኑ መሆናቸውን ይቆጣጠራል፡፡መ/ቤቱን በሚመለከት በሚነሱ የህግ ጉዳዮች ጥያቄዎች ላይ ተገቢውን ማብራሪያና ምላሽ እንዲሠጥ ያደርጋል፡፡ የህግ ጥሰሰት የተፈጸመባቸው ጉዳዮች እንዲለዩና ክስ እንዲመሰረትባቸው መደረጉን ይከታተላል፣ መፍትሄ ማግኝታቸውን ያረጋግጣል፡፡
ለሙስናና ብልሹ አሰራር ቀደዳ የሚከፈቱ የተቋሙ አዋጆች፤ ደንቦች፤ መመሪያዎች እና ማኑዋሎች እንዲሻሻሉ ያደርጋል፤ ተግባራዊነቱ ይከታተላል ። በአሰራር ማንዋልና የመተዳደሪያ ኮዶፍ ኢቲክስ እንዲሁም በሌሎች አጠቃላይ ሀገር አቀፍ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና ፖሊሲዎች ዙሪያ የተቋሙ ማህበረሰብ የግንዛቤ እንዲያገኙ መድረክ እንዲመቻች ያደርጋል፤
በተቋሙ ውስጥ ሃብታቸውንና የገንዘብ ጥቅማቸውን እንዲያስመዘግቡ የህግ ግዴታ የተጣለባቸውን የተቋሙ ሰራተኞችና ሃላፊዎች ሃብትና የገንዘብ ጥቅሞች በአግባቡ እንዲያስመዘገቡ በማድረግ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል፡
ከስነ-ምግባርና ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን ተቀብሎ ትክክለኛነታቸው እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤ ጥቆማዎቹ ትክክል መሆናቸው ሲረጋገጥ ምርመራ እንዲካሄድ ያደርጋል፣ ከስነ-ምግባርና ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የተወሰዱ ዕርምጃዎችን ይከታተላል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የወጡ ፖሊሲዎች፣መመርያዎችና ደንቦች እንዲዘጋጁ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ግንዘቤ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ የሚዘጋጁ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ፕሮግራሞችና እቅዶች ትግበራ ላይ የኤች አይ ቪ/ኤድስ፣ አካል ጉዳተኞችን አረጋውያንና አካባቢ ጥበቃ ጉዳይ መካተቱን ያረጋግጣል፡፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚንቀሳቀሱ አጋር አካላት ጋር በዘላቂነት በትብብር ለመሥራት መድረኮችን ያዘጋጃል፣ መግባቢያ ሰነዶችን ይፈራረማል፣ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የገቢ ማስገኛ ስልት ይቀይሳል፣ ሃብት ያፈላልጋል፡፡ የተገኘውን ፈንድ አገልግሎት ላይ የሚውልበትን መንገድ ይቀይሳል፣ ይከታተላል፣ አፈፃፀሙን ይገመግማል፡፡