ጳጉሜ 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
****************®***************
የኢትዮጵያ ደን ልማት አመራሮችና ሰራተኞች “የኅብር ቀን” የኢትዮጵያ ማንሰራራት በሚል መሪ መልእክት ዛሬ ጳጉሜ አራት በልዩ ልዩ የሁነት ዝግጀቶች ተክብሯል፡፡
ኢትዮጵያ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ የጳጉሜ ቀናትን በተለያዩ ስያሜዎችና መሪ መልእክቶች የህዝቡን ተነሻሽነት፣ አንድነት፣ ተሳትፎንና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በልዩ ልዩ የሁነት ዝግጀቶች እያከበረች ትገኛለች፡፡
የ2018 ዓ.ም የጳጉሜ ቀናት አከባበር ጳጉሜ አንድ “የእምርታ ቀን”፣ ጳጉሜ ሁለት “የማንሰራራት ቀን”፣ ጳጉሜ ሶስት “የፅናት ቀን”፣ ጳጉሜ አራት “የኅብር ቀን” እና ጳጉሜ አምስት “የነገ ቀን” በማለት በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ደን ልማት አመራሮችና ሰራተኞች ጳጉሜ አራት “የህብር ቀን” ምክንያት በማደረግ “የብዝኃነት ፀጋው፣ ተግዳሮቶችና ኮሙኒኬሽን ሚና” በሚል ርዕስ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡

