ሰኔ 28፣ 2018 (ኤፍ.ቢ.ሲ/ው.ኢ.ሚ)
አዲስ አበባ
***************®****************
ዓለማችንን በአሁኑ ወቅት እየፈተኑ ከሚገኙ ጉዳዮች መካከል የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተላቸው ጫናዎች በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። ኢትዮጵያ ውሃን ጨምሮ ለተፈጥሮ ሃብት የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት ምላሽ ለመስጠት ተግባራዊ ርምጃ በመውሰድ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች።
ከእነዚህ ተግባራት መካከል ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ የሚገኘው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ሲሆን፤ በመርሐ ግብሩ ስኬት ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ስሟ በጉልህ እንዲጠቀስ አድርጓል።
በመንግሥት ቆራጥነት እየተተገበረ ያለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የኢትዮጵያውያንን ልብና ጉልበት በአንድነት ያስተሳሰረ ታላቅ ሀገራዊ ተግባር ሆኖ ቀጥሏል።
ይህ በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በይፋ የተጀመረው መርሐ ግብር ዛፍ ከመትከል ባሻገር ውሃን ጨምሮ ለተፈጥሮ ሀብቶች ዋስትና የሰጠ ውጤት አስመዝግቧል

