በግብርና ሚኒስቴር በአዲሱና በቀድሞው ሚኒስትር መካከል የስራ ርክክብ ተደረገ

በግብርና ሚኒስቴር የቀድሞው ሚንስትር አቶ ዑመር ሁሴን ለአዲሱ የግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር ለዶ/ር ግርማ አመንቴ የስራ ርክክብ አደረጉ፡፡ በዚህም ባለፉት አራት ዓመታት የተሰሩ ዋና ዋና የግብርና ስራዎች ላይ አቶ ዑመር ሁሴን ገለጻ አድርገዋል፡፡ በመሆኑም ጥሩ ውጤት የተመዘገበባቸው ዋና ዋና ስራዎች እና ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚስፈለጉ ቦታዎችን በመጥቀስ ገልጸዋል፡፡ በዚህም ግብርናው ባለፉት አመታት በስንዴ ምርት፣ በአርንጓዴ አሻራና መሰል ስራዎች ጥሩ ውጤት እንዳስመዘገበ ተገልጿል፡፡ ይህንን ይበልጥ ለማዘመንና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በኢንቨስትመንትና በመካናይዜሽን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንዳለበት ተገልጿል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ በምርጥ ዘር አቅርቦት፣ በመስኖ ስራ፣ እንዲሁም ተጨማሪ ግብርናውን አጋዥ የሆነ ፋይናንስ…

Read More