የአረንጓዴ አሻራ የደን ሸፋን ከማሳደግ በላይ… – Ethiopian Broadcasting Corporation | Facebook

የአረንጓዴ አሻራ ከደን ሸፋን ማሳደግ በላይ መሆኑን በኢቲቪ ዳጉ የውይይት መርሐ ግብር ላይ እንግዳ የነበሩት የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳሬክተር አቶ ከበደ ይማም ገልጸዋል።
አረንጓዴ አሻራ እንደ ሀገር ጠንካራ ኢኮኖሚ የመገንባት እንዲሁም ጠንካራ ሀገረ መንግስት የመገንባት መሰረትም ነው ብለዋል።
አረንጓዴ አሻራ የተራቆቱ መሬቶችን እንዲያገግሙ ከማድረግ ባሻገር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ሰፊ የሆነ ድርሻ እንዳለው ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ ለሀገር ሉዓላዊነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለውም ጠቅሰዋል።
“የተራቆቱ መሬቶችን እንዲያገግሙ ማድረግ ካልቻልን፤ የምናልመው ምርታማነት አይኖርም፣ ብዝኃ ህይወት ያልቃል ብሎም እንደ ውኃ ያሉ ተፈጥሯዊ ሀብቶቻችን ይቀንሳሉ፤ ይህም በሂደት አስከፊ ለሆነ ችግር ይዳርገናል” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ።
ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት የተገበረችው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርም ይህንኑ አስከፊ ችግር ቀድሞ ለመከላከል የተተገበረ እና ውጤት የተመዝገበበት እንደሆነም አንስተዋል።
የአፍሪካ አጀንዳ 2063 ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ማህበረሰብ እና የማይበገር ኢኮኖሚ መፍጠር አላማው ያደረገ እቅድ መያዙንም አንስተው፤ ከዚህም መካከል 22 በመቶ የኢትዮጵያ ድርሻ መሆኑን በመጥቀስ አህጉራዊ ድርሻችን ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።
ይህን ግብ እውን ለማድረግ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳሬክተር አቶ ከበደ ይማም
በንፍታሌም እንግዳወርቅ

Related posts