በግብርና ሚኒስቴር በአዲሱና በቀድሞው ሚኒስትር መካከል የስራ ርክክብ ተደረገ

በግብርና ሚኒስቴር የቀድሞው ሚንስትር አቶ ዑመር ሁሴን ለአዲሱ የግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር ለዶ/ር ግርማ አመንቴ የስራ ርክክብ አደረጉ፡፡ በዚህም ባለፉት አራት ዓመታት የተሰሩ ዋና ዋና የግብርና ስራዎች ላይ አቶ ዑመር ሁሴን ገለጻ አድርገዋል፡፡ በመሆኑም ጥሩ ውጤት የተመዘገበባቸው ዋና ዋና ስራዎች እና ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚስፈለጉ ቦታዎችን በመጥቀስ ገልጸዋል፡፡ በዚህም ግብርናው ባለፉት አመታት በስንዴ ምርት፣ በአርንጓዴ አሻራና መሰል ስራዎች ጥሩ ውጤት እንዳስመዘገበ ተገልጿል፡፡ ይህንን ይበልጥ ለማዘመንና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በኢንቨስትመንትና በመካናይዜሽን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንዳለበት ተገልጿል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ በምርጥ ዘር አቅርቦት፣ በመስኖ ስራ፣ እንዲሁም ተጨማሪ ግብርናውን አጋዥ የሆነ ፋይናንስ ማፈላለግ ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው ባለፉት አመታት ግብርና ዘረፍ ውስጥ የሰሩ መሆናቸው ጠቅሰው ይህንን ተቋም በበላይነት እንዲመሩ በመደረጉ እድለኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ከነበረበት ደረጃ ባለፉት አራት አመታት አንድ እርምጃ ተሻግሯል በቀጣይም አሁን ካለበት ሦስትና አራት እጥፍ በማሳደግ ግብርናውን መለወጥ ይጠበቅብናል በማለት አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም ግብርና አንዱ የኢኪኖሚ ሞተር በመሆኑ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ዘርፎችም ወሳኝ ዘርፍ መሆኑን በመረዳትና ሌሎችም እንዲረዱት በማድረግ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ይህንም በተገቢው ተረድቶ የእለት እለቱን በመስራት የተሻለ ደረጃ ማድረስ ከሁሉም አካላት ይጠበቃል በማለት ተናግረዋል፡፡
All reactions:

27

2
Like

 

Comment
Share

Related posts