


በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ኢትዮጵያ ለበርካታ ሐገሮች ምሳሌ መሆን መቻሏን የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር አቶ ከበደ ይማም ገለፁ፡፡
የመሬት መራቆት እና የአየር ንብረት ለውጥ በስነ ምህዳር ላይ አሉታዊ ተዕፅኖ እየሳረፈ በመሆኑ መንግስታት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በየአመቱ የሚሰሩ ብዙ ጥናቶች በጉዳዩ ላይ ትኩረት አድርገው ሰፊ መረጃዎችን እንደሚያወጡም ገልፀዋል፡፡
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ የሰጠችው ትኩረት በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ለበርካታ ሀገሮች ምሳሌ እንድትሆን ያስቸላት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም መንግስት ለተራቆቱ አከባቢዎች ማገገሚያ የሚውል ፈንድ ማፅደቁን ተከትሎ የደን ጭፍጨፋው ወደ 27 ሺህ ሔክታር መሬት ዝቅ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የተገኘው ለውጥ ከምንጊዜውም በላይ የላቀ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገር በቀል ዝርያዎች ላይ ትኩረት በማድረግ፣ በየዓመቱ ሀገር በቀል ችግኞች የማፍላት ስራ እየተሻሻለ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
