ዛፍን በመትከል አለማችንን የተሻለች በማድረግ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማምጣት ይቻላል፡፡ ዛፍን በአግባቡ ከያዝነው ቁሳቁስና የተለያዩ ግልጋሎቶችን በመስጠት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይሰጠናል፡፡ ዛፍ ከጠፋ ቀጣይነት ያለው ህይወት ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ የዛፎች መኖር የህልውና ዋስተና ናቸው፡፡ ደን ሊሻሻል፣ ሊያድግ እና ሊጠበቅ የሚችል ታዳሽ የሆነ ሃብታችን ነው፡፡ ዓለምን የተሻለች ለማድረግና ለማስቀጠል ዛፍን እንደመትከልና መንከባከብ የመሰለ አስደሳችና ቀላል ዘዴ የለም፡፡ በ1992 በተደረገው የመሬት ጉባኤ (Earth Summit) ብዝሀ ሕይወት፤ የአየር ንብረት ለውጥና በረሃማነት ጉዳይ ጀምሮ ስለደን በተደጋጋሚ ትኩረት እንዲሰጠው የተወሰነ ሲሆን በተለይ በ2012 በተደረገው የሪዮ ስብሰባ የዓለም መንግስታት የተቀናጀ የዘላቂ ልማት በኢኮኖሚ በማህበራዊ እና በአካባቢያዊ ዘርፎች እንዲረጋገጥ…
Read More