(ወቅታዊ መልዕክት) 12 ጥር 2012: ደን በተለያዩ ነገሮች ተፅዕኖ ሊደርስበት ይችላል፡፡ በአለም ዙሪያ ከፍተኛ ችግር ከሚያደርሱ ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው ደግሞ የሰደድ እሳት ነው፡፡ በአለም ደረጃ በየዓመቱ በሰደድ እሳት በብዙ ሺህ ሄክታር የሚደርስ ደን የሚወድም ሲሆን በኢትዮጵያም እሰከ መቶ ሺህ ሄክታር ደን ላይ ጉዳት እንደሚደርስ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የቃጠሎው መንስዔ የተለያየ ቢሆንም በኢትዮጵያ በአብዛኛው ሰው ሰራሽ ችግር ነው፡፡ ሰዎች የእርሻ ማሳቸውን ለማዘጋጀት በሚያደርጉት የማቃጠል ሂደት እና በጫካ ማር ቆረጣ ሂደት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንደሆኑ የተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ በኢትዮጵያ ከጥር እስከ መጋቢት ባሉት ነፋሻማና ሞቃት የአየር ሁኔታ በሚጠናከርበት ወቅት የደን ቃጠሎ በብዛት ይከሰታል፡፡ …
Read More