SPIN (Science Policy Information Network) Africa

የኢትዮጵያ ደን ልማት ከዓለም አቀፍ የደን ምርምር ህብረት ተቋም (IUFRO) ጋር በመተባባር ከተለያዩ ሀገራት የተጋበዙ የደን ሳይንቲስቶች የሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ የቦርድ አባላት ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
የዓለም የደን ምርምር ድርጅቶች ዩንዮን (IUFRO) በ1892 እ.ኤ.አ. በጀርመን ኤበርስዋልዴ የተመሠረተ እና ዋና መሥሪያ ቤቱ በኦስትሪያ ቪየና ከተማ የሚገኝ፣ በደን ሳይንስ ዘርፍ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆነ የትብብር መረብ ነው።
ዩንዮኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ120 በላይ አገሮች ውስጥ ከሚገኙ 630 የሚጠጉ አባል ድርጅቶች የተውጣጡ ከ15,000 በላይ ተመራማሪዎችን አሰባስቧል።
የዩኒየኑ ከፍተኛ አመራሮች በአፍሪካ እየተከናወኑ ያሉ ደን ነክ ምርምሮችን ለፖሊሲ አውጭዎችና አስፈፃሚዎች ለማድረስ SPIN (Science Policy Information Network) Africa የተሰኘው አለማቀፋዊ ውይይት ከመስከረም 25 እስከ 30/2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል፡፡
ስብሰባውን በይፋ የከፈቱት በኢትዮጰያ ደን ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዳመነ ዳሮታ እንዳሉት “ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የተጎዳ መሬትን መልሶ እንዲያገግም ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት በማድረገጓ በሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግም ማደረጓን ጠቅሰው የአፍሪካ አጠቃላይ እድገት ውጤታማ ሊሆን የሚችለው በምርምር የተደገፉ ስራዎች ወደ ተግባር መቀየር ሲችል በመሆኑም የአፍሪካ የሳይንስና የፖሊሲ መረጃ ኔትወርክ በሚደረገው ውይይት ላይ የሚመነጨውን የፖሊሲ አማራጭ ለመተግበር ኢትዮጵያ ቁርጠኛ” መሆኗን አስረድተዋል፡፡
የ “SPIN Africa” አስተባባሪና የዓለም የደን ምርምር ድርጅቶች ዩንዮን (IUFRO) የአፍሪካ ተወካይ ዶክተር ውባለም ታደሰ የእኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንዳሉት “ይህ አለማቀፋዊ ስብሰባ ዋና ዓላማው በሳይንቲስቶችና በህግ አውጭዎች መካካል ጠንካራና ዘላቂ የግንኙነት ስርዓት በመዘርጋት በደን ዘርፍ የማህበረስቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡
በኮንጎ ሪፕብሊክ የደን ኢኮኖሚ ሚኒስትር ሮሳይሌ ሞታንዶ በበኩላቸው “ሳይንስቶች የአፍሪካን ህዝብ ከችግር የሚያወጣና ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ተጨባች የምርምር ውጤት ማፍለቀና ተደራሽ ማድረግ ከተቻለ” መንግስታቸው ለመተግበር ዝግጁ መሆኑ ገልፀዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት የደን ፎረም ሴክሬተሪ ጁሊያት ባየው እንደገለፁት “የተጎዱ መሬቶች እንዲያገግሙ እና ደኑ መስጠት የሚገባውን ጠቀሜታ እንዲሰጥ ያለሳይንሳዊ እውቀት፣ የማህበረሰብ ልምድን ባለካተተና በግልፅ ባልተነጋገረበት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተግባራትን ቢፈፅሙም ውጤታማ ሊሆኑ ስለማይችሉ ሳይንሳዊና ተግባራዊ እውቀትን፣ የተመራማሪዎችና የህግ አውጭዎችን ግንኙነት በመዘርጋት በዘርፉ የሚታዩ የእውቀት ክፍተቶችን በመሙላት ዘላቂና የተቀናጀ ስራን በመስራት የተሻለች ዓለምን መፍጠር ይኖርብናል” ብለዋል፡፡ በውይይቱ የሰባት ሀገራት የዘርፉ ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው፡፡
Scroll to Top