የዓለም አቀፍ የደን ምርምር ህብረት ተቋም (IUFRO) አመራሮች በኢትዮጵያ ደን ልማት ጉብኝት

ከመስከረም 25 እስከ 30/2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ SPIN (Science Policy Information Network) Africa ውይይት ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ደን ልማት በመገኘት በልማቱ እና በምርምር ዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ተሞክሮዎችን በመመልከት ገለፃና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡
በእለቱ የልኡካን ቡድኑ የተቋሙን የላብራቶሪ መሰረተ ልማትና እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን በዘርፉ ባለፉት አመታት ስለተሰሩ ስራዎችና ያሉባቸውን ክፍተቶች አስመልከቶ ዶክተር አለማየሁ ኢሳያስ በኢትዮጵያ ደን ልማት የምርምር ማዕከላት አስተባበሪ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የልምድ ልውውጡን ልኡካን የመሩት የዓለም አቀፍ የደን ምርምር ህብረት ተቋም (IUFRO) ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ዳኔላ ክሊንችሚት በተደረገላቸው አቀባበልና ኢትዮጵያ ለዘርፉ የሰጠቸው ትኩረት እና ህዝቡን በማነቃነቅ ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኝ መትከል መቻሏ ለሌሎች ሃገሮች አርያነት ያለው መሆኑን በማድነቅ ገልፀው ለወደፊት አብረው ለመስራትና በሚጠየቁት ሁሉ አቅማቸው የቻለውን ሞያዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን በተቋማቸው ስም ቃል ገብተዋል፡፡
ውይይቱን ተከትሎ ባለፉት ዓመታ ኢትዮጵያ 56 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ህዝቡን እንዴት ማንቀሳቀስ እንደተቻለ እና ሌሎች ተዛማች ጉዳዮችን አስመልከቶ ጥያቄዎች ከደን ተመራማሪዎቹ ልኡካን ተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ ደን ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዳመነ ዳሮታ፣ በኢትዮጵያ ደን ልማት የሰው ሰራሽ ደንና አረንጓዴ አሻራ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አበሩ ጠና እና በዶክተር አለማየሁ ኢሳያስ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶበታል
፡
Scroll to Top