የኢትዮጵያ ደን ልማት ባለሙያዎች በቻይና የደንና ግራስ ላንድ ተቋም ጋባዥነት ያገኙትን የአጭር ጊዜ ስልጠናና የተግባር ምልከታ “የምርምር-ለልማት” ሲምፖዚየም ላይ ቀርቦ ውይይት ተካሄደ፡፡
በኢትዮጵያ ደን ልማት የሰው ሰራሽ ምርምር ዳይሬክተር ዶ/ር አባይነህ ደረሮ በመደበኛው “የምርምር-ለልማት” ሲምፖዚየም ላይ ያገኙትን የአጭር ጊዜ ስልጠናና የተግባር ምልከታ ተሞክሮዎችን ስኬት ለኢትዮጵያ ደን ልማት ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች አካፍለዋል፡፡
ዶክተር አባይነህ ያገኙትን ልምድ “የምርምር-ለልማት” ሲምፖዚየም ላይ ሲያካፍሉ እንደገለፁት “ቻይና የደን ልማትን የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከምግብ ዋስትና፣ ከገጠር ልማት፣ ከድህነት ቅነሳ እና ከአካባቢ መልሶ ማቋቋም ጋር በማቀናጀት ሰፊ ስራዎችን ማከናወኗ ጠቁመዋል።
የደን ሽፋንን በማሳደግ የአፈርና ውሃ ጥበቃን ማጠናከር፣ የመሬት ለምነትን ማሻሻልና የግብርና ምርታማነትን መደገፍ በደን ልማትና በምግብ ዋስትና መካከል ያለውን ትስስር ለህብረተሰቡ፣ ለአካባቢው፣ የኢኮኖሚና የምግብ ዋስትና ጥቅሞችን በአንድነት ማምጣት እንደተቻለ በተሞክሮ ልውውጣቸው ስኬታማ እንደነበር” ገልፀዋል;;
