የሠንደቅ ዓለማ ቀን

የብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማችን በህገ መንግስት ተደንግጎና ቀኑ ደግሞ በየአመቱ ተከብሮ እንዲውል በአዋጅ ቁጥር 863/2006 ጥቅምት ወር በገባ የመጀመሪያው ሰኞ እዲከበር ተደንግጎ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የሠንደቅ ዓለማ ቀን በየዓመቱ በልዩ ልዩ ዝግጀቶች የሚከበር ሲሆን ዘንድሮ ለ19ነኛ ጊዜ “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!” በሚል መሪ መልዕክት በሀገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት ተከብሯል።
በዚሁ ሀገራዊ ማዕቀፍ መሠረት በአሉ በኢትዮጵያ ደን ልማት አመራሮችና ሠራተኞች በድምቀት ተከብረ የዋለ ሲሀን እለቱ በሞቀ ብሄራዊ መዝሙር፣ በቃል መግባት፣ በሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ሁነትና በንግግር መልዕክት ማስተላለፍ እንዲሁም ሠራተኞች እለቱን ቀልጣፋ አገልግሎት ለዜጎች በክብር በመስጠት አክብረውታል።
የብሔራዊ የሠንደቅ ዓለማ ቀን ሲከበር በንግግር መልእክት ያስተላለፉት በኢትዮጵያ ደን ልማት የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሰብሰቤ እንዳሉት “የሠንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር “ሀገራችንን በመውደድ፣ ዜጎችን በኩራት በማገልገል፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጠናክረን በመጠበቅ እና የሀገራችንን ብልፅግና ሊያረጋግጡ በሚችሉ ሀገራዊ ጥረቶች ላይ የበኩላችንን ድርሻ በማበርከት መህን አለበት” ብለዋል። ሀላፊዋ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁት “ሰንደቅ ዓላማችን የህዝባችን የጋራ ማንነት፣ የሉዓላዊነት ማኅተም እና የትውልድ አደራ በመሆኑ በውስጣችን ያለውን በማንኛውም ሀገራዊ ፈተና ጊዜም አብረን በጋራ እንድንቆም የሚያስተሳስረን ብሔራዊ ዐርማችንና ነው” ብለዋል፡፡
በበአሉ ላይ የተሳተፉ ሰራተኞች የቀኑን መከበር አስመልክቶ ለስራ ክፍላችን እንደተናገሩት “ሰንደቅ አላማችን የአብሮነታችንና የሉአላዊነት መገለጫችን በመሆኑ በየቀኑ ልናከብረው፣ ልንጠብቀውና በመስዋዕትነታችንም ጭምር አፅንተነው ልንኖር ይገባል ለዚህ አንዱ መገለጫ ደግሞ ሁላችንም መደበኛ ስራችንን በቅንነት፣ በታማኝነትና በሀገራዊ ኩራት ልንፈፅመው ይገባል” ብለዋል።
Scroll to Top