በቀርካሃ ላይ ሲሰራ የነበረው የላብራቶሪ የምርምር ስራ የተራቆቱ ቦታዎችን ቶሎ እንዲያገግሙ ማድረግ የሚያስችል ነው

EEFRI, 04/11/2020, Addis Ababa

የኢትዮጵያ የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት ከአማራ መልሶ ማቋቋም ልማት ድርጅት (አመልድ) እጽዋት ቲሹ ካልቸር ላብራቶሪ ጋር በመተባበር ላለፉት ሁለት አመታት የቆላ ቀርከሃን በብዛት ለማባዘት የሚያስችል ፕሮቶኮል ለማውጣት የተደረገው ምርምር ውጤታማ ሆኗል፡፡

በዓለማችን ከ1600 በላይ የቀርከሃ ዝርያዎች ሲኖሩ በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የሆኑ የቆላና የደጋ የሚባሉ ሁለት የቀርከሃ ዝርያዎች እንዳሉ መረጃዎች ያሰረዳሉ፡፡

ቀርከሃ በዘሩ መራባት የሚችል ቢሆንም ፍሬውን ለማግኘት በረጅም አመት አንድጊዜ የሚያብብ በመሆኑና በተለያዩ ተባዮችና በሽታዎች ምክንያት በአንድ ጊዜ ብዙ ዘር ለማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡

በመሆኑም በተለያየ ሰው ሰራሽ ምክንያት የተጎዳውን ቆላማ ቦታ በቆላ ቀርከሃ ለመሸፈን የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት የቆላ የቀርካሃ ችግኝን በእጽዋት ቲሹ ካልቸር ላብራቶሪ ችግኝ በብዛት ለማብዛት ሲደረግ የነበረው የምርምር ስራ ውጤታማ መሆን ችሏል፡፡

ይህንን ፕሮቶኮል በመጠቀም የተራቆተውን የአባይ ተፋሰስ የተወሰነውን ቦታ በቆላ ቀርከሃ ለመሽፈን እጽዋቱ በብዛት እየተባዛ ይገኛል ፡፡

እነዚህ የሚባዙ ችግኞችን በኢትዮጵያ የአካባቢ፡ ደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ድጋፍ ከሰላሌ እና ከደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር የህዳሴው ግድብ በደለል እንዳይሞላ የተወሰነውን የሸለቆውን ክፍል እንዲያገግም በማድረግ ለአካባቢ ጥበቃ ከሚሰጠው ጠቀሜታ በተጨማሪ የቆላ ቀርከሃ ቶሎ የማደግ ባህሪ ስላለው የአካባቢውን ወጣቶች በማደራጀት የተለያዩ የቀርካሃ ምርት ውጤቶችን በማምረት ተጠቃሚ ለማድግ የሚያስችል ስራ ነው።

Related posts