ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ረገድ ያስመዘገበቻቸውን ታላላቅ ሀገራዊ ስኬቶችና የአረንጓዴ ልማት ጥረቶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማካፈል በCOP31 ጉባኤ ላይ ስኬቷን ይዛ ተሳትፎ ታደርጋለች።
ሀገራችን ዘላቂና አየር ንብረትን የሚቋቋም የወደፊት ጊዜን በመገንባት ረገድ የበኩሏን ድርሻ ለማበርከትና ሀገራዊ ራዕይዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማንፀባረቅ ሙሉ ዝግጅቷን አጠናቃለች።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር እና በታዳሽ ኃይል ልማት ሚናዋን ያረጋገጠችው ኢትዮጵያ በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ የምታደርገው ተሳትፎ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞዋን የሚያፋጥንና የአየር ንብረት ፍትሕን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ዓለም አቀፍ ጥረት ይበልጥ የሚያጠናክር ይሆናል።
“በፅኑ የአየር ንብረት እርምጃ ዘላቂና አረንጓዴ የወደፊት ጊዜን እንገነባለን!
የሰው ዘር መገኛ፣ የጽናትና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት፣ የጉባኤውን ትክክለኛውን የኮፕ 32 ይፋዊ ድረ-ገጽ (https://cop32ethiopia.et/) በመጎብኘት አሁናዊ መረጃዎችንና ዝግጅቶችን መከታተል ይቻላል።