አረንጓዴ ዐሻራ፡ የምግብ ዋስትና የጀርባ አጥንት።

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19
2018 (ኤፍ ኤም ሲ)
****************®****************
የአየር ንብረት መለዋወጥ፣ የአፈር ምርታማነት መቀነስ እና የደን ሽፋን መሳሳት በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርትና ምርታማነት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡
በተለይም ግብርና የኢኮኖሚያቸው የጀርባ አጥንት ለሆነ የአፍሪካ ሀገራት ምርታማነት ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ይህንን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቋቋም እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከምትከውናቸው ተግባራት መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዋነኛው ነው።
ይህ ንቅናቄ የደን ሽፋንን ለማሳደግ የሚደረግ ዘመቻ ብቻ ሳይሆን፤ የተፈጥሮ ሀብትን መልሶ በማልማት የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና በዘላቂነት ለማረጋገጥ የተነደፈ ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪካዊ ዐሻራ ነው፡፡
ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተከናወኑ ሥራዎች በርካታ የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ በማድረግ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ከፍተኛ ሚና አበርክተዋል።
መርሐ ግብሩ የአፈር መሸርሸርን በመከላከል፣ የደረቁ የውሃ አካላትን ዳግም በመመለስ እና የአፈርን ምርታማነት በመጨመር ለአርሶ አደሩ ምቹ የእርሻ መሬት እንዲኖር አስችሏል።
በመርሐ ግብሩ ከሚተከሉ ችግኞች መካከል አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ ፣ የቡና እና የቅመማ ቅመም ችግኞች የሚገኙ ሲሆን፤ ይህም ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ ተጨማሪ የምግብና የገቢ ምንጭ ሆነዋል።
አርሶ አደሩ ከተለመዱት የእህል ሰብል ዝርያዎች በተጨማሪ እነዚህን የፍራፍሬ ምርቶች በማልማቱ የቤተሰቡን የስነ ምግብ ልምምድ ማሻሻል ችሏል።
መርሐ ግብሩ ችግኝ ከማፍላት ጀምሮ በተከላና በእንክብካቤ ሥራዎች ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡
በተጨማሪም የእጽዋት ብዝሃ ሕይወት በከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ በማድረግ በንብ ሀብት ልማት በማር ምርት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡
በዚህም አርሶ አደሩ ዘመናዊ የአመራረት ዘዴዎችን በመጠቀም ከፍተኛ ጥራት ያለው የማር ምርት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ እንዲሁም ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንዲችል አድርጓል፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ከተፈጥሮ ጥበቃና ኢትዮጵያን አረንጓዴ ካባ ከማልበስ ባለፈ ሀገርን ከጥገኝነት ነጻ በማውጣት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እውን የሆነ ታሪካዊ ትልም ነው።
የዚህ ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ምንም የፎቶ መግለጫ የለም።.

ተዛማጅ ልጥፎች