የቆላ ቀርከሃን ለማባዘት የሚያስችል ፕሮቶኮል ለማውጣት የተደረገው ምርምር ውጤታማ ሆኗል

ኤፍሪአይ, 04/11/2020

ኢንስቲትዩታችን (የኢትዮጵያ የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት)ከአማራ መልሶ ማቋቋም ልማት ድርጅት (አመልድ) እጽዋት ቲሹ ካልቸር ላብራቶሪ ጋር በመተባበር ላለፉት ሁለት አመታት የቆላ ቀርከሃን በብዛት ለማባዘት የሚያስችል ፕሮቶኮል ለማውጣት የተደረገው ምርምር ውጤታማ ሆኗል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ፕሮቶኮሉን በመጠቀምና ችግኝ በማምረት በተለያየ ሰው ሰራሽ ችግር ምክንያት በተራቆተው የአባይ ተፋሰስ የሚገኘውን የተወሰነውን ቦታ በቆላ ቀርከሃ ለመሽፈን እጽዋቱ በብዛት እየተባዛ ይገኛል ፡፡

ማስታዎሻ፤ የቆላ ቀርከሃ ቶሎ የማደግ ባህሪ እና ለኢኮኖሚያውና ለአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው እፅዋት ነው። ይሁን እንጅ ቀርከሃ ለማበብና ዘር ለማፍራት ከ20 – 120 ዓመታት ያላነሰ ጊዜ ይፈልጋል። ሌላው ችግር ከአበበና ከአፈራ በኋላ በአንድ ጊዜ የመሞት እድሉ ከፍተኛ መሆኑ ነው። ይህ የምርምር ውጤት ችግሩን በእጅጉ እንደሚቀርፍ ይታመናል።

ኢኤፍአሪ ከአመልድ ቲሹ ባህል ላብራቶሪ ጋር በመተባበር የሎውላንድ የቀርከሃ ችግኞችን በብዛት ለማምረት የሚያስችል ፕሮቶኮል አዘጋጅቷል. ችግኞቹ በአባይ ወንዝ ተፋሰስ ይተከላሉ, በሰው ሰራሽ ምክንያቶች የሚዋረድ.

ማስታወሻ: የሎላንላንድ ቀርከሃ በፍጥነት እያደገ ነው, ለኢኮኖሚ እና ለአካባቢ ጥበቃ እና መልሶ ማቋቋም ከፍተኛ ጥቅሞች አሉት. ቀርከሃው ከ ይወስዳል 20-120 ለማበብ እና ፍሬ ለማፍራት እና በጅምላ ሲሞቱ. ይህ የምርምር ውጤት እንደነዚህ ያሉትን ተግዳሮቶች በከፍተኛ ሁኔታ ለመቋቋም ይረዳል.

ተዛማጅ ልጥፎች