ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ለበርካታ ሀገሮች ምሳሌ መሆን ችላለች

በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ኢትዮጵያ ለበርካታ ሐገሮች ምሳሌ መሆን መቻሏን የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር አቶ ከበደ ይማም ገለፁ፡፡ የመሬት መራቆት እና የአየር ንብረት ለውጥ በስነ ምህዳር ላይ አሉታዊ ተዕፅኖ እየሳረፈ በመሆኑ መንግስታት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በየአመቱ የሚሰሩ ብዙ ጥናቶች በጉዳዩ ላይ ትኩረት አድርገው ሰፊ መረጃዎችን እንደሚያወጡም ገልፀዋል፡፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ የሰጠችው ትኩረት በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ለበርካታ ሀገሮች ምሳሌ እንድትሆን ያስቸላት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም መንግስት ለተራቆቱ አከባቢዎች ማገገሚያ የሚውል ፈንድ ማፅደቁን ተከትሎ የደን ጭፍጨፋው ወደ 27 ሺህ ሔክታር መሬት ዝቅ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ…

ተጨማሪ ያንብቡ

የአረንጓዴ አሻራ የደን ሸፋን ከማሳደግ በላይ… – የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን | ፌስቡክ

የአረንጓዴ አሻራ ከደን ሸፋን ማሳደግ በላይ መሆኑን በኢቲቪ ዳጉ የውይይት መርሐ ግብር ላይ እንግዳ የነበሩት የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳሬክተር አቶ ከበደ ይማም ገልጸዋል። አረንጓዴ አሻራ እንደ ሀገር ጠንካራ ኢኮኖሚ የመገንባት እንዲሁም ጠንካራ ሀገረ መንግስት የመገንባት መሰረትም ነው ብለዋል። አረንጓዴ አሻራ የተራቆቱ መሬቶችን እንዲያገግሙ ከማድረግ ባሻገር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ሰፊ የሆነ ድርሻ እንዳለው ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ ለሀገር ሉዓላዊነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለውም ጠቅሰዋል። “የተራቆቱ መሬቶችን እንዲያገግሙ ማድረግ ካልቻልን፤ የምናልመው ምርታማነት አይኖርም፣ ብዝኃ ህይወት ያልቃል ብሎም እንደ ውኃ ያሉ ተፈጥሯዊ ሀብቶቻችን ይቀንሳሉ፤ ይህም በሂደት አስከፊ ለሆነ ችግር ይዳርገናል” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። ኢትዮጵያ ላለፉት…

ተጨማሪ ያንብቡ