የአረንጓዴአሻራ የተጎዱ መሬቶች ማገገሚያ ፈንድ

#የአረንጓዴአሻራ የተጎዱ መሬቶች ማገገሚያ ፈንድ
See Translation
የጸደቀው ረቂቅ አዋጅ የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን በደን ልማት መልሰው እንዲያገግሙ ያደርጋል።
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ደን ልማት ትናንት ታኀሣሥ 15 2017 ዓ.ም የጸደቀውን የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አሥተዳደር ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም የጸደቀው ረቂቅ አዋጅ በኢትዮጵያ የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን በደን ልማት እና በጥምር ደን ግብርና መልሰው እንዲያገግሙ ያደርጋል ብለዋል። ከፍተኛ የኾነ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ ምህዳራዊ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ገልጸዋል።
ለዓለም ፈተና እየኾነ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል እንደ ሀገር የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለአየር ንብረት ለውጥ መልስ የሰጠ እና ኢትዮጵያ በ2023 ወደ አየር የምትለቀውን ጋዝ ለመቀነስ የገባችውን ቃል እውን ለማድረግ ወሳኝ መንገድ መኾኑንም አንስተዋል።
የጸደቀው ልዩ ፈንድ የተለያዩ ዓላማዎች እንዳሉትም ገልጸዋል። በተለይም ለሴቶች እና ወጣቶች በቋሚነት የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል ዘርፍ መኾኑንም ዋና ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
ዘጋቢ: ቤቴል መኮንን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Related posts